
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያመጣች የባሕር ዳር ከተማ እንቁ አግኝተናል።
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዋ ሶሊያና ማሩ ከ600 ውስጥ 437 በማምጣት ስኬት አስመዝግባለች፡፡ በመጣውም ውጤት በእጅጉ መደሰቷን ገልጻለች።
ለውጤቱ መሳካት የቤተሰቦቿ ያልተቆጠበ ድጋፍ፣ የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እና የመምህራን ልዩ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብላለች።
”አካል ጉዳተኝነት ፈጣሪ የሰጠኝ ጸጋ ነው” ያለችው ተማሪ ሶሊያና አልችልም ብሎ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም፤ የሚመጡ ፈተናዎች በሙሉ መሸጋገሪያዎች ናቸው በማለት ለሌሎች ተማሪዎች እና ጓደኞቿ ጥንካሬ የሚኾን መልእዕት አስተላልፋለች።
የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን በሕግ ትምህርት ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላትም ተናግራለች፡፡ ወደ ትምህርት ቤት በምትመላለስበት ጊዜ የሚገጥማትን የእግር መንገድ ድካም ለማቃለል በኤሌክትሪክ (በዘመናዊ ሞተር) የሚሠራ ዊልቼሮች ድጋፍ እንዲደረግላትም ጥሪዋን አቅርባለች።
#ባሕር_ዳር #መስከረም_08_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፡- ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
