
የምዕራብ ጎጃም ዞን አሥተዳደር ሲያካሂድ የቆየውን የመንግሥት እና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አጠናቅቋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ዕድሜዓለም አንተነህ እንደገለጹት በመንግሥት እና በፓርቲ የሚከናወኑ ተግባራት ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እና ቅቡልነት እንዲኖራቸው መትጋት ያስፈልጋል።
የታቀዱ የልማት አና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ውጤታማ እንዲኾኑ መዋቅራዊ መግባባትን መፍጠር እንዲሁም የመሪዎችን፣ የባለሙያዎችን እና የሕዝቡን አንድነት ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለፈው በጀት ዓመት ኅብረተሰቡን ያሳተፉ የሰላም ግንባታ ሥራዎች በመከናወናቸው በአካባቢው የተሻለ ሰላም ማስፈን መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም በተለይ በግብርናው ዘርፍ በክላስተር የልማት ሥራዎችን በማከናወን ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ያስቻለ መኾኑን አብራርተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም የተጠናከረ የሰላም ማስከበር ሥራ በማከናወን የኅብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም ተመላክቷል።
የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር መሪዎች በተሳተፉበት በዚህ የመዝጊያ መድረክ በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ዕውቅ እና ሽልማት ተበርክቷል።
#አሚኮ #ምዕራብጎጃም #ልማትናሰላም #መዋቅራዊመግባባት #አማራክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹
#ፍኖተ_ሰላም #መስከረም_07_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
