‎በተከናወነው የሰላም ማስከበር ተግባር አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን አድርጓል።

2


‎በደቡብ ጎንደር ዞን «አርቆ ማየት፤ አልቆ መሥራት» በሚል መሪ መልዕክት ሲካሄድ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተጠናቅቋል።

‎የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ እንደገለጹት ባለፈው በጀት ዓመት የተገኘውን ልምድ በመጠቀም በቀጣይ በሰላም እና ደኅንነት ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሠራል።

‎መዋቅራዊ አሠራሮችን እስከ ታችኛው የመንግሥት መዋቅር ማውረድ እና ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ጎንደር ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መንበር ክፈተው በበኩላቸው ታጥቀው በጫካ የሚንቀሳቀሱ ኀይሎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ የማድረግ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

‎ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን የተከናወነው የሰላም ማስከበር ተግባር አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረጉንም አብራርተዋል።

‎በመድረኩ የተሳተፉ መሪዎች በመልካም አሥተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ለሕግ ማስከበር ሥራዎች ቅድሚያ እንደሚሰጡ እና የጸጥታ መዋቅሩን እንደሚደግፉም አረጋግጠዋል።

‎ሰላምን ዘላቂ ለማድረግም የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

‎ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ይህ መድረክ በቀጣይ በጀት ዓመት የታቀዱ የልማት እና የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በጋራ መግባባት ለመፈጸም አቅጣጫ በማስቀመጥ እና ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎች የዕውቅና ሽልማት በመስጠት ተጠናቋል።

‎#አሚኮ #የዕቅድ_ትውውቅ #አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

‎#ደብረ_ታቦር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም

‎ዘጋቢ:- ተክለብርሃን ፈንታ

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ቴክኖሎጂ እና ፈጠራን ያማከሉ ሥራዎችን በከፍተኛ ደረጃ መፈጸም ለነገ የማይባል ተግባር ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next articleየባሕር በር ጉዳይ በሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲያዊ መርህ እልባት እንዲያገኝ የምሁራን ጥረት ወሳኝ ነው።