‎በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመማር ማስተማር ሥራ ተጀመረ።

6
‎‎በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ባንጃ ወረዳ አስኩና አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የብሔረሰብ አሥተዳደሩ እና የባንጃ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ‎‎የባንጃ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ፀሐይነህ ቦጋለ የትምህርት ዘመኑን በስኬት ለማጠናቀቅ የተማሪ፣ የወላጆች እና የትምህርት ቤቶች ትስስር መጠናከር እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
‎‎ተማሪዎች የወደፊት ሕይወታቸው የተቃና እንዲኾን በርትተው መማር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ‎‎የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው ዓለሙ የትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያው ቀን የመማር ማስተማር ሥራ አስፈላጊ የኾኑ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀው መጀመሩንም ተናግረዋል።
‎‎ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ወደ ትምህርት ቤት በመላክ የሚፈጠረውን የትምህርት ጊዜ ብክነት ማስቀረት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
‎‎በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በትምህርት ዘመኑ ከ476 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“በአዲሱ የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል” የደሴ ከተማ ተማሪዎች
Next article“የትምህርት ጥራት እና የትውልድ ግንባታ ቀዳሚ አጀንዳችን ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ