
የምሥራቅ ጎጃም ዞን አሥተዳደር “አርቆ ማየት፤ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ መልዕክት የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት ያጋጠሙ ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር በሰው ሃብት ልማት፣ በተቋም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም በኢኮኖሚና ልማት ዘርፎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
አክለውም የመሪዎች እና የባለሙያው የመፈጸም አቅም ማደግ ለሕዝቡ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ወሳኝ በመኾኑ በቀጣይም ተቋማት ተቀናጅተው እና ተናበው በመሥራት ስኬቱን ማስቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ በላይ በበኩላቸው ያለፉ ተግዳሮቶችን እና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን በመለየት በ2019 በጀት ዓመት የጋራ ግንዛቤ እና ቁጭት በመያዝ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ዕቅዱ የትኞቹን ችግሮች እንደሚፈታ እና የዞኑን ጸጋዎች በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
#አሚኮ #ዕቅድ_ትውውቅ_ምሥራቅጎጃም #አማራክልል ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_05_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
