በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ተጀመረ።

2

 

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን “የመጀመሪያው ቀን፣ የመጀመሪያው ክፍል” የመማር ማስተማር ሂደት መጀመሩን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ኀላፊ ሰይፈ ሞገስ እንደገለጹት ትምህርት መስከረም 05/2019 ዓ.ም ለመጀመር ቀድሞ በቂ ዝግጅት በመደረጉ በታቀደለት ጊዜ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስጀመር ተችሏል።

ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት አሟልተው በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲገኙ ያሳሰቡት የመምሪያው ኀላፊ ወላጆችም ትምህርት መጀመሩን ተረድተው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #ትምህርት #አማራክልል_ዋግኽምራ ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_05_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየሰው ልጅ በሰራሽ አስተውሎት ሊሸነፍ ይችላል?
Next article‎የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው።