
የምዕራብ ጎጃም ዞን ”አርቆ ማየት አልቆ መሥራት” በሚል መሪ መልዕክት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸምን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን እየገመገመ ነው።
የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ዕድሜዓለም አንተነህ በጀት ዓመቱ በርካታ ችግሮችን በማለፍ ፈተናዎችን ወደ ድል የተቀየረበት መኾኑን ገልጸዋል።
የታሪካዊ ጠላቶችን እኩይ አላማ ለማክሸፍ ከፌዴራል እና ከአካባቢው የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ መከናወኑንም አንስተዋል።
የነበሩ ጉድለቶችን ለመሙላት እና ሕዝቡ የሰጠውን አደራ ለመወጣት በፍጥነት መትጋት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በ2019 በጀት ዓመት ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር፣ ለሕዝብ ዋጋ መክፈል እና የአካባቢን ፀጋ አሟጦ መጠቀም ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ያለፈው በጀት ዓመት ሥር ሰዶ የቆየውን ጽንፈኝነት በመዋጋት ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት መኾኑን አንስተዋል።
በተለይም ከሰላም ማጽናት ሥራ ባሻገር የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት መደረጉንም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
