
የደቡብ ወሎ ዞን “አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ መልዕክት በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲ እና በመንግሥት በተከናወኑ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እያካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን በበጀት ዓመቱ የዞኑ ሰላም እንዲረጋገጥ በማድረግ እና የጽንፈኞች ምኞትን በማክሸፍ በኩል በትኩረት መሠራቱን ገልጸዋል። ይሁንና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ላይ አሁንም ክፍተቶች መኖራቸውን ነው የተናገሩት። በቀጣይም በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኘው እንደ ፓርቲ ሰላም እና ልማትን የሚያፋጥኑ ተግባራት ላይ በትኩረት ሢሠራ መቆየቱን አንስተዋል። በምርጫው ላይ በተሠራው ስኬት ተገኝቷል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- መሐመድ በቀለ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
