የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች ይሠራሉ።

5
የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2019 የዕቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ዘርፉ ለክልሉ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን ተቋማት አስተባብሮ የያዘ ነው ብለዋል።
የውይይት መድረኩ በዘርፉ ስር የሚገኙ ተቋማት በ2018 በጀት ዓመት የነበራቸውን አፈጻጸም በመገምገም በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ለመፈጸም የሚያስችል ተሞክሮ የሚወሰድበት መኾኑንም አብራርተዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ቅንጅታዊ አሠራሮችን ተግባራዊ በማድረግ፣ የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎችን በማጠናከር ውጤታማ ተግባራት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። ተቋማት ተመሳሳይ የመፈጸም አቅም እያዳበሩ መኾኑንም አንስተዋል።
በ2019 በጀት ዓመት በገጠር ዘርፍ ስር ያሉ ተቋማት ባለፈው ዓመት የነበሩትን ችግሮች በመቅረፍ የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች እንደሚሠሩም አመላክተዋል።
ለዚህም ተቋማት የነበሩ ድክመቶችን በማረም፣ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ ጠንካራ የክትትል እና ድጋፍ ሥርዓትን በማጠናከር የጋራ ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ጋሻው ሙጨ (ዶ.ር) እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት የፕሮጀክት እና የኢኒሸቲቭ ሥራዎችን መሠረት በማድረግ እና በግቦች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ስኬታማ ሥራዎች ተሠርተዋል።
ለዚህም የጋራ ግልጽነት በመፍጠር፣ ችግሮችን በመለየት፣ ለችግሮች የጋራ መፍትሔ በመስጠት፣ ባለቤት በመኾን እና በቁርጠኝነት ወደ ተግባር መገባቱ የመጣ ውጤት መኾኑን አንስተዋል።
የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤ የመሬት ቢሮው ከሌሎች ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን እና ትብብርን መሠረት በማድረግ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል።
በቀጣይም በዘርፉ የተሻለ ለመፈጸም የሚያስችሉ ግብዓቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article‎የምዕራብ ጎንደር ዞን “አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ ሀሳብ ግምገማና ውይይት እያካሄደ ነው።
Next articleሰላም እንዲረጋገጥ በትኩረት ተሠርቷል።