
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ”አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ መልዕክት የፓርቲ እና የመንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ በ2018 በጀት ዓመት የውስጥ ሰላምን ለማረጋገጥ እና ከአጎራባች ወንድም ሕዝቦች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የተሠራው ሥራ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በ2018 በጀት ዓመት የሕዝብን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ በርካታ ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናልም ብለዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሕመድ ሁሴን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመሪዎችን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት በሥልጠና ለማብቃት ጥረት የተደረገበት ዓመት መኾኑን ጠቁመዋል።
በክፍለ ኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንደሚሠራም አመላክተዋል።
የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች በ2018 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ጉድለቶችን በመሙላት በተያዘው በጀት ዓመት የሕዝብን የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሠራ መኾኑን አሥረድተዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
