
”አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መልዕክት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች
አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መድረክ መካሄድ መካሄድ ጀምሯል። በመድረኩም የብሔረሰብ አስተዳደሩ፣ የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ አመራሮች እየተሣተፉ ነው።
ባለፈው በጀት ዓመት ተደራራቢ ችግሮችን ተቋቁመን ስኬቶችን አስመዝግበናል ያሉት የብሔረሰብ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዳግም ባይነሳኝ ናቸው።
አመራሩ ቅንጅታዊ አሠራርን ይበልጥ ማሣደግ የሚያሥችሉ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ማሥቻላችን የስኬቶች መመዝገብ ቀዳሚ ምክንያቶች እንደሆኑም አክለዋል።
በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ተሞክሮ በመቀመር የማሥፋት ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠቆሙት ኃላፊው በበጀት ዓመቱ ግልፅ፣ ተጨባጭና አካባቢያዊ ፀጋዎችን መሠረት ያደረገ እቅድ በማቀድ ለውጤታማነቱ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የባለፈው በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በብሔረሰብ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አበባ ወርቁ እየቀረበ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
