የሕዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ሰፊ ጥረት ተደርጓል።

8
የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ”አርቆ ማዬት አልቆ መስራት” በሚል መሪ መልዕክት የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትጋትና ጥረት የሚጠይቅ፣ የተናበበ አመራርነትን የሚሻ እንደኾነ አንስተዋል።
እንደ ሀገር በርካታ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎች ቢበዙም በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት የፈጸመ እና የኢትዮጵያን ሕልውና ያስቀጠለ መሪ እና ሕዝብ ድህነት እና ኋላቀርነትን ታሪክ ለማድረግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት። ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ከተማ ለመገንባት አርቆ ማየት እና አልቆ መሥራት ይገባል ብለዋል።
የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ፈታኝ የጸጥታ ሁኔታዎችን በመጋፈጥ የሕዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ሰፊ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
እንደ ከተማ የመልካም አሥተዳደር ችግርን የሚፈታ የተገልጋዩን እንግልት የሚቀንስ የሞሰብ አንድ ማዕከል አገለግሎት መገንባቱ ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ መጠናቀቁን፣ የከተማውን እና ዙሪያ ወረዳዎችን የኃይል መቆራረጥ በዘላቂነት የሚፈታ የመብራት ሰብስቴሽን ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እና ሌሎች የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን አንስተዋል።
በግንባታ ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች ጨምሮ ሌሎች ሥራዎችን አልቆ ለመሥራት መሪዎች እና ሕዝቡ መቀናጀተ ይገባቸዋል ብለዋል። ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሰላምን በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article‎በተያዘዉ በጀት ዓመት የዞኑን ማኅበረሰብ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል።
Next article‎ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ሕዝቡን የልማቱ ተጠቃሚና ተሳታፊ የማድረግ ሥራ ይተገበራል።