
በሰሜን ሸዋ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በደብረብርሃን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ዞኑ በ2018 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም በክልል ደረጃ የሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የአመራሩ ቁርጠኝነትና የመናበብ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
የተገኘው ውጤት በ2019 በጀት ዓመት በሕዝብና በመንግሥት የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት ትልቅ ስንቅ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን እንደ መነሻ በመጠቀም በተያዘዉ በጀት ዓመት የዞኑን ማኅበረሰብ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
ሕዝቡን የሚመጥን የተሟላ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞንየ2018 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ እየተደረገ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ በዞኑ የሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ዮናስ ታደሰ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
