የምሥራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

4
ድጋፉን ለተማሪዎች አስረክበው ንግግር ያደረጉት በምሥራቅ ዕዝ ስር የክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል መሐመድ እንድሪስ እንዳሉት የክፍለ ጦሩ አባላት ከግዳጅ በተጓዳኝ በበጎ አገልግሎት ሥራዎች ላይም እየተሳተፉ ነው። ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች መሆናቸውን በማሰብ የክፍለ ጦሩ አባላት ካላቸው ላይ ቀንሰው በማገዝ የዜግነት ድርሻቸውን እየተወጡ ስለመኾኑም ተናግረዋል።
በመሆኑም 50 ደርዘን ደብተር እና 10 ፓኬት እስክሪብቶ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል። ከአከባቢው መሥተዳደር ጋር በመነጋገር የትምህርት መርጃ ቁሳቁሰ ለመግዛት የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን በመለየት ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲጠናከሩ እና በትጋት በመማር ለስኬት እንዲበቁ ሚናው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
የእስቴ ወረዳ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ኮማንደር እህትትሁን ተማች ሠራዊቱ መተኪያ የሌለዉ ሕይወቱን ከፍሎ ሰላምን ከማረጋገጥ እና ሀገርን ከማፅናት ባሻገር በትውልድ ግንባታ ላይ የሚያደርገውን የነቃ ተሳትፎ አድንቀዋል።
መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
ባሕር ዳር #መስከረም04/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየጥምር ጦሩ የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።
Next articleድርቅን የሚቋቋሙ ስድስት አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች ተለቀቁ።