የጥምር ጦሩ የማድረግ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

6
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ በወረዳው ግዳጃቸውን እየፈጸሙ ከሚገኙ የጥምር ጦሩ መሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የዞብል ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል አይቸው ወንድሜነህ እንዳሉት በጥምር ጦሩ በተሠራ ውጤታማ ኦፕሬሽን የአካባቢው የሰላም ሁኔታ እጅግ መልካም የሚባል ሁኔታ ላይ መገኘቱን አብራርተዋል።
ወረዳውም አሁን ለደረሰበት የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ የጥምር ጦሩ በቅንጅት መሥራት እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ መኾኑን ተናግረው በተለይ የሚኒሻውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አዱኛ አዳሙ በበኩላቸው በቡሬ ዙሪያ ወረዳ እና በቡሬ ከተማ የተሰማራው የጥምር ጦር የማድረግ አቅም ለሌሎች ዞኖች እና ወረዳዎች መልካም ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደኾነ ገልጸዋል።
ኮማንደር አዱኛ አያይዘውም የጽንፈኛው ቡድን ከዚህ በፊት ይሞክረው የነበረውን የፊት ለፊት ውጊያ በመተው ሰርጎ የመግባት እና የተናጥል እንቅሰቃሴ ማድረግ ቢጀምርም በጥምር ጦሩ የተቀናጀ ምት እየፈረሰ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
እንደ ምሥራቅ ዕዝ መረጃ ከኾነ በቡሬ ዙሪያ እና በቡሬ ከተማ የተሰማራው ጥምር ጦር የማድረግ አቅም፣ ቅንጅታዊ አሠራር፣ ወታደራዊ ቁመና እንዲሁም የሥነ ልቦና ግንባታው በእጅጉ የተሻለ መኾኑን የገለጹት ደግሞ በውይይት መድረኩ አስተያየት የሰጡት ተሳታፊ መሪዎች ናቸው።
ባሕር ዳር #መስከረም_03/2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“መስከረም” የምድር እፎይታ፣ የሰው ልጅ አዲስ ተስፋ”