ሰላምን የሚጠበቀው በሁሉም ዜጎች የጋራ ሥራ ነው።

2
የምሥራቅ ዕዝ ኮር አመራሮች በደብረ ታቦር ከተማ የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ከከተማዋ ባጃጅ ሾፌሮች እና የፀጥታ አካላት አመራሮች ጋር ዉይይት አድርገዋል።
የምሥራቅ ዕዝ ኮር አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ ሰላም ማስጠበቅ የሚገባው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ብቻ ሳይኾን ሁሉም በመተባበር ነው ብለዋል። ሰላም ተጠብቆ እንዲቀጥል የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሚናቸው የጎላ ስለመኾኑም ጠቁመዋል። ለወደፊትም በአካባቢው እየተሽሎኮሎኩ የቀጣናውን ሰላም ለማወክ የሚመጡ ተላላኪዎችን በንቃት በመከታተል እና ለሚመለከተዉ አካል በመጠቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አድማ መከላከል ፖሊስ ሻለቃ አዛዥ ኮማንደር ይገርማል ፍቃዱ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ትልቅ የዕድገት ጎዳና ላይ በመሆኗ ይህ አካባቢም ልማቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል ይችል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል መተባበር ይገባል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ያለው ዘለቀ በተከታታይ ዓመታት የአካባቢው ማኅበረሰብ በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ሲዘርፉ የነበሩ ተላላኪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል። የከተማውንና የማኅበረሰቡን ሰላም እንዲቀጥል እያደረግን እንገኛለን፤ ወደፊትም ይህንን ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት መምሪያ ኀላፊ አዳነ ደምሴ እንዳሉት ባጃጆችን እና ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ተገቢውን ስምሪት በማድረግ ለማኅበረሰቡ በተገቢዉ መንገድ እንዲያገለግሉ ከማድረግ ባለፈ ሕገ ወጥ ሥራዎች የሚሠሩ የጥፋት ኃይሎችን በመጠቆም ሹፌሮች የበኩላቸዉን እየተወጡ መኾኑን አብራርተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ብሩክ ልዑል ሰላም ለሁሉም ነገር አስፈላጊ በመሆኑ ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግሯል።
መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነው።
ባሕር ዳር #መስከረም03/2018 ዓ.ም
Previous articleየምሥራቅ ዕዝ ሠራዊት አባላት ሕግን በቀጣይነት በማስከበር ሕዝቡ በሰላም እንዲያለማ እያስቻሉ ነው።
Next articleመስከረም እና የልጅነት ቦርሳ