የምሥራቅ ዕዝ ሠራዊት አባላት ሕግን በቀጣይነት በማስከበር ሕዝቡ በሰላም እንዲያለማ እያስቻሉ ነው።

7
በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች ሕግ የማስከበር ግዳጁን እየፈጸመ የሚገኘው የምሥራቅ ዕዝ ኮር አንድ ሬጅመንት በየአካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የጽንፈኛው ቡድን አባላት ላይ በወሰደው ርምጃ ለልማት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው።
ሬጅመንቱ ስልታዊ የፀረ-ሽምቅ ኦፕሬሽን በመሥራት ኅብረተሰቡን ከዝርፊያ፤ ከግድያ እና እገታ መታደጉን የሬጅመንቱ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዓባይነህ ፈለቀ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ሬጅመንት አዛዡ ገለጻ ሠራዊቱ በተሰማራባቸው በአዊ እና አካባቢው በሚገኙ ውፍቲ ዳጢ፣ አባድራ፤ ጭሮ፤ ጫራ፤ ሮብ ገበያ፤ ዋሻ፣ አፈር ማፈሻ፣ ወንዳፋይ፣ አፄ ዮሐንስ ተራራ፤ አፋፍ ኢየሱስ እና ወለተጴጥሮስ ገዳም በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ታጥቆ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ላይ ከነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው የፀረ-ሽምቅ አና የደፈጣ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ቁሳዊ እና ሰብአዊ ኪሳራ በማድረስ በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉን አብራርተዋል፡፡
በተደረገው ኦፕሬሽን 16 የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን 22 የድሽቃ ጥይት፣ 60 የብሬን ጥይት ከነ ሸንሸሉ፣ 4 የብሬን ሸንሸል፣ 5 የአጅ ቦንብ፣ 6 ክላሽ፣ 4 ኋላቀር መሳርያ፣ 2 የወገብ እና የደረት ትጥቅ መገኘቱን እና በርካታ የሎጀስቲክስ ንብረት መውደሙን ገልጸዋል፡፡
የምሥራቅ ዕዝ ሠራዊት ከሕዝቡ እና ከጥምር ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በፅንፈኛ ቡድኑ እና ተላላኪዎቹ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነው።
ባሕር ዳር #መስከረም03/2018 ዓ.ም
Previous article🌽🌾ወርቃማው መስከረም እና የጸደይ እሸት
Next articleሰላምን የሚጠበቀው በሁሉም ዜጎች የጋራ ሥራ ነው።