ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ።

12

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሕንድ ይፋዊ የሥራ ጉብኝቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በመገናኘት፣ የኢትዮጵያ-ሕንድ አጋርነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ሃሳብ ተለዋውጠናል ብለዋል።

‎ውይይታችን የመከላከያ ትብብርን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን አጋርነት ማጠናከር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ነው ያሉት። እነዚህ መስኮች በተግባር የታገዘ ትብብራችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና ለሕዝቦቻችን አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም አላቸው።

‎ኢትዮጵያ እና ሕንድ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር፣ የዘመናት የባሕል ግንኙነት እና በሕዝቦቻችን መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አለን። ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉት በርካታ አቅሞች ገና ያለተነኩ ናቸው። ያለንን የጋራ ታሪክ እና ትብብር በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት፣ በኢንቨስትመንት፣ በዘላቂ ልማት እና ይበልጥ በጠነከረ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ወደተመሠረተና የላቀ የጋራ ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥ አጋርነት ለመለወጥ አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።

‎🇪🇹 🇮🇳

Previous article🌻”በበዓል ወቅት ሳይቀር በቁርጠኝነት መሥራታችሁ ለስኬት ያበቃችኋል” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next article‎አዲስ ዓመትን በአደይ አበባ፤ አፈሙዝን በሰላም ካባ መቀበል።