🌻”በበዓል ወቅት ሳይቀር በቁርጠኝነት መሥራታችሁ ለስኬት ያበቃችኋል” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

19

 

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ አዲስ ዓመትን በማስመልከት በምክር ቤቱ ግቢ በእድሳት ሥራ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ማዕድ አጋርተዋል።

ዋና አፈ ጉባኤዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት በበዓል ወቅት በሥራ ላይ መገኘታችሁ የሚያኮራ ነው። ይህም የኢትዮጵያ የሥራ ባሕል እየተቀየረ መምጣቱን ያሳያል ነው ያሉት።

የወደፊት ሕይወታችሁን ስኬታማ ለማድረግ በበዓል ወቅት ሳይቀር በቁርጠኝነት መሥራታችሁ ለስኬት ያበቃችኋል ብለዋል።

ስኬታማ ለመኾን በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ማዕድ ማጋራቱ የሠራተኞችን የሥራ ትጋት ለማበረታታት እና ለአዲሱ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ያለመ መኾኑን ተናግረዋል።

በበዓላት ከሚደረግ ድጋፍ ባሻገር የመረዳዳት ባሕልን እሴት ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

#አሚኮ #ማዕድ_ማጋራት #አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_01_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🌻 ከዓለም የምትለየው የ13 ወራት ባለቤቷ ኢትዮጵያ