
”ስኬቶቻችንን የሞራል ስንቅ አድርገን በአዲሱ ዓመት የላቀ ውጤት ለማምጣት በቁጭት እንተጋለን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፦
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!!
አዲስ ዓመት የበለጠ ተስፋ የምንሰንቅንበት፣ ቂምና ጥላቻን በይቅርታ ሽረን በአብሮነት የምንሻገርበት ጊዜ ይሁንልን።
አዲሱ ዓመት ለመጪው ትውልድ አሻራ የምናስቀምጥበት፤ ያለንን ዕምቅ የመልማት ፀጋ ከሕዝባችን አቅም ጋር አቀናጅተን በመጠቀም ልማታችን የምናፋጥንበት ዓመት ይሆናል።
ዘላቂ ሰላማችንን አፅንተን፤ አብሮነታችንና ትብብራችንን ካጠናከርን ከፊት ለፊታችን አዲስ ድልና ስኬት ይጠብቀናል። ለዚህም ቃላችን ጠብቀን የተሻለ ዘመን ለመፍጠር አልቀን እንሠራለን።
ስለሆነም ያጋጠሙንን ሳንካዎች ተሻግረን፤ ጉድለቶቻችንን አርመን፤ ስኬቶቻችንን የሞራል ስንቅ አድርገን በ2019 ዓ.ም የላቀ ውጤት ለማምጣት በቁጭት እንተጋለን።
አዲሱ ዓመት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ትብብራችን እና አብሮነታችን የበለጠ የሚጠናከርበት፤ የእድገትና የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት!
#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_05_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
