“በይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

18
በይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች ካለፈው መንገድ በመማር የወደፊቱን መንገድ የሰላምና የዴሞክራሲ መንገድ ያደርጉታል ተብሎ ተስፋ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለ2019 አዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ላይ እንደገለጹት፣ ወደ ሀገራዊ ምክክር የመጡ ልዩ ልዩ ወገኖች በአንድም በሌላም ስሕተት የታሠሩ ወገኖች በይቅርታ እና በህግ አግባብ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር።
መንግሥት ይሄንን ተቀብሎ በሂደቱ የተስማሙትን ፈትቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የምክክሩም ዓላማ ኢትዮጵያውያን በጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ የተግባቡባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲያቀርቡ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥትም ለምክክሩ ሐሳቦች ትግበራ ያለውን ቁርጠኝነት በዚህ የይቅርታ ሂደት ማሳየት ጀምሯልም ነው ያሉት።
በዚህ የይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል ብለዋል።
ማኅበረሰቡም እነዚህ ወገኖች በሀገር ሰላምና ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ማገዝና መምከር እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
#ameco,bahirdar
Previous articleለሕጻናቱ እና ለአረጋውያኑ ደስታ እየተሠራ ነው።