
ኢትዮጵያ ታላላቅ ተግባራትን የከወነችበት 2018 ተሰናበተ። አዲሱ 2019 ዓመት ያለፉትን ዓመታት ተግባራት የምናጸናበትና የምናሰፋበት፤ አዳዲሶቹን ደግሞ የምንወጥንበት ዓመት ነው።
ባሳለፍነው ዓመት ሀገራዊ ምክክሩን ማሳካታችን ቀጣዩ ዓመት በሁሉም ረገድ የተሻለ እንዲሆን አድርጎታል። የምክክሩንም ውጤት ከወዲሁ ማጣጣም ጀምረናል።
ቀጣዩ 2019 የፖለቲካው ምኅዳር የበለጠ ይሰፋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ ፍሬ ያፈራል። በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በዲጂታል ዘርፎች ያመጣናቸው ውጤቶች የኢትዮጵያን መሪነት ያጠናክሩታል።
የባሕር በር ለማግኘት የጀመርነው ጥረት ፍሬ ማፍራት ይጀመራል።
ብዙዎች ዐማጽያን በሰላምም በሌላም መንገድ ወደቀናው ጎዳና ይመጣሉ። በ2019 የኢትዮጵያ ታሪክ የበለጠ ማርሹን ይቀይራል።
መንግሥት፣ ሕዝብና የፖለቲካ ኃይሎች በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ አንድነት ፈጥረን የኢትዮጵያን እመርታ እውን እናድርግ።
2019 የሰላም ፣ የብልጽግና እና የእመርታ ይሁንልን።
