
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
በይቅርታ እና በምክክር የጀመርነውን ብሩህ ጉዞ የምናጸናበት፣ ኢትዮጵያን እያስቀደምን በቀጥተኛው ርቱዕ መንገድ የምንጓዝበት የሰላም፣ የፍቅር፣የአንድነት እና የስኬት ዘመን ይኾንልን ዘንድ እመኛለሁ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
