የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ስኬታማ ጉዞ

7
✍️ የአረንጓዴ ዓሻራ መርሐ ግብር በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሲበሰር እንደ ሀገር ያጋጠሙ በርካታ የዘላቂ ልማት ተግዳሮቶችን (ለምሳሌ የመሬት መጎሳቆል፣ የደን እና ብዝኃ ሕይወት መጨፍጨፍ የውኃ አካላቶቻችን መድረቅ እና የቀሩትም በደለል መሞላት የወጣቶች ስደት ለድርቅ ተጋላጭንተ…) ለመከላከል ታስቦ ነበር።
✍️ መርሐ ግብሩ በመጀመሪያው ምዕራፍ 50 ቢሊዮን ችግኝ በማኅበረሰብ ተሳትፎ ለመትከል አቅዶ ተነሳ።
✍️ በስምንት ዓመታት ኢትዮጵያ 56 ነጥብ 8 ቢሊዮን (በዚህ ዓመት ብቻ 8 ነጥብ 2ቢሊዮን )ችግኝ በመትከል በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ጽፋለች።
✍️ አጠአቃላይ ከተተከሉ ችግኞች ከ3 ቢሊየን በላይ የሚኾኑት በአንድ ጀምበር የተተከሉ ናቸው። ይህም በዓለምም ላይ ታሪክ ኾኖ ተጽፏል።
✍️ ከተተከሉ ችግኞች 60 በመቶ የሚኾኑት የጥምር ደን ግብርና (ፍራፍሬ ቡና የመኖ ዝርያዎች ናቸው 35 በመቶ የደን ዝርያ ናቸው)።
✍️ ይህ ታላቅ የልማት ድል የተሳካው ለመርሐ ግብሩ በተሰጠው ቁርጠኛ አመራር ነው።
✍️ ይህ የመንግሥት መዋቅር ትኩረት በዓመት ከ25 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ማንቀሳቀስ ችሏል።
✍️ እስካሁን በተሠራ ሥራ የደን ጭፍጨፋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
✍️ በእርሻ ማሳ ያለ የአፈር ክለት ከ130 ቶን ሄክታር በዓመት ወደ 54 ቶን በዓመት ቀንሷል። ወደ ውኃ አካላት የሚገባ የአፈር ደለል ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ቶን በዓመት ወደ 208 ሚሊዮን ቶን ቀንሷል።
✍️ በመርሐ ግብሩ ወደ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚጠጋ አረንጓዴ ሥራ ለወጣቶች እና ለሴቶች ፈጥሯል።
✍️ በርካታ አካባቢ የፍራፍሬ እና የደን ኩታገጠም እየተፈጠረ የገበሬው የኢኮኖሚ ዋስትና እየኾነ መጥቷል።
✍️ ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲወዱ፣ እንዲቆረቆሩ እና እንዲተባበሩ እያደረገ ነው።
✍️ እንደ ሀገር ትልቅ የልማት መርሐ ግብር ቀርጸን መተግበር እንደምንችል ትልቅ ተሞክሮ የወሰድንበት እና ለዓለምም ያሳየንበት ነው።
✍️ በተለይ እንደ አየር ንብረት ለውጥ፣ የበረሃማነት መስፋፋት አይነት ካሉ ከዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ጋር ተያይዞ ሀገራችን ሰለባ ብቻ ከመኾን የመፍትሔው አካል መኾኗን ለዓለም ያሳየችበት መርሐ ግብር ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሰላም ፍላጎት፣ ተስፋ እና የትውልድ አደራ በነገው ቀን
Next articleእርስ በእርስ የመረዳዳት ባሕልን የሚያጠናክሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።