በጋራ ልማት እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ነገ እንሻገራለን።

7
የኢትዮጵያ የብቃት እና ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የጳግሜን 5 የነገው ቀንን አስመልክቶ የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አካሂዷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ጣሰው እንዳሉት ተቋሙ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ሲሠራ ቆይቷል። አዲሱ ዓመትም ተቋሙ የሪፎርም ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ሥራ የገባበት ወቅት ላይ በመኾኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።
ዛሬ ላይ የነገው ቀን ሲከበር ያለው ለሌለው በማካፈል ዝቅተኛ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ነው ብለዋል።
የነገ ኢትዮጵያ እውን የሚኾነው ሀገርን ያሻገሩ አረጋውያንን በመደገፍ እና በማመሥገን መኾኑን አንስተዋል።
ኢንስቲትዩቱ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶችን በሥልጠና ብቁ እንዲኾኑ የሚያደርጉ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን አውስተዋል። በደም ልገሳ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በትምህርት ቤት ግንባታም ተቋሙ ተሳትፎ አድርጓል ነው ያሉት።
ተቋሙ የ2019 አዲስ ዓመትን በማስመልከትም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የተቋሙ ሠራተኞች ማዕድ አጋርቷል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“2019 ዓ.ም በአንድነት ቆመን ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት የምንጥልበት ዓመት ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ
Next articleየአማራ ክልል ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ቴክኖሎጂ እንዲኾን እየተሠራ ነው።