
በሀረሪ ክልል የጳጉሜን 5 “የነገ ቀን” መርሐ-ግብር የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በመርሐ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት የዘመን መለወጫ መልዕክት፣ የአዲስ ዓመት መባቻ ያለፈውን ገምግመን፣ አዲሱን ዓመት በላቀ የተስፋ እና የሥራ መንፈስ የምንቀበልበት አጋጣሚ መኾኑን ገልጸዋል።
የተጠናቀቀው የ2018 ዓ.ም በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት ልዩ እና ታሪካዊ ዓመት እንደነበር ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን ጠቅሰው የሚከተሉትን ዋና ዋና አበይት ኩነቶች አጉልተዋል፦
ዛሬ ግን ያ የጨለማ ዘመን አብቅቶ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመከባበር ባሕላችን እየተመለሰ፣ እንደ ነውር ይታይ የነበረው ወንድማማችነት እና የጋራ ማንነታችን እያበበ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም የቋንቋ፣ የባሕል እና የታሪክ ብዝኀነት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን እና ለጋራ ብሔራዊ ትርክታችን ውበት መኾናቸውን አብራርተዋል።
አክለውም የፀረ-ሰላም ኀይሎችን እኩይ እንቅስቃሴ በማክሸፍ፣ ተቋማትን በማጠናከር እና የሕዝብን ጥያቄዎች በትክክል በመመለስ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
“2019 ዓ.ም ሀገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት፣ የሕግ የበላይነትን የምናረጋግጥበት እና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት የምንጥልበት ዓመት ይኾናል” ያሉት አቶ ኦርዲን በመሪዎች እና በሕዝቡ መካከል የተፈጠረውን የአንድነት እና የመነሳሳት ማዕበል አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፍተኛ አደራ ያለ በመኾኑ “ለአፍታም የምንተኛው እንቅልፍ አይኖርም” ሲሉ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
