ትምህርትን መደገፍ ሀገር አሻጋሪ ትውልድን መፍጠር ነው።

5
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አዲስ ዓመትን አስመልክቶ ቤተሰቦቻቸው በገቢ ዝቅተኛ ለኾኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለኾኑ የተቋሙ ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) መንግሥት ሰው ተኮር ተግባርን የሚያከናውን በመኾኑ አዲሱ ትውልድ የሀገር ፍቅር እንዲኖረው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
ተቋሙ በተለያየ ጊዜ በገቢ ዝቅተኛ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ሲያደርግ እና የመኖሪያ ቤት ሲያድስ መቆየቱን አንሠተው በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ድጋፉ ተማሪዎች እና ሠራተኞች በአዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ ይዘው በትምህርታቸው፣ በሥራቸው ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲኾኑ ለማስቻል ያለመ መኾኑን ተናግረዋል።
ተማሪዎችን ማገዝ ትውልድን ማነጽ መኾኑንም አንስተዋል። የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል፤ ግብዓት እንዲሟላ፤ ውጤታማ የትምህርት ሥርዓት እንዲኖር እና የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ግብር ወሳኝ በመኾኑ ማኅበረሰቡ በአዲሱ ዓመት በታማኝነት ግብር እንዲከፍልም አሳስበዋል።
ታማኝ ግብር ከፋይ ሲኖር የትምህርት ጥራት ይረጋገጣል፤ መሠረተ ልማቶች ይገነባሉ፤ ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ሀገርን ማስረከብ ይቻላል ነው ያሉት። ትምህርትን መደገፍ ሀገር አሻጋሪ ትውልድን መፍጠር ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሰላማን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ለበጎነት የተዘረጉ የሠራዊቱ እጆች በፍኖተ ሰላም
Next article“የነገው ቀን በዛሬው ብርታታችን፣ ጥረታችን እና መስዋዕትነታችን የሚመሠረት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ