
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጳጉሜን አምስት የነገውን ቀን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት፣ ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባሕላችን እየኾነ ነው ብለዋል።
ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል፣ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ነው፣ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል ነው ያሉት።
በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መኾኗን በኩራት ያበስራል ብለዋል በመልዕክታቸው።
