ማዕድ ማጋራት፦ ከምግብ ባሻገር ፍቅር እና ክብር

6

ማዕድ ማጋራት፦ ከምግብ ባሻገር ፍቅር እና ክብር

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ አጋርቷል።

በማዕድ ማጋራቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለው ለሌለው እንዲያካፍል በማድረግ የተጀመረው በጎ ባሕል አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። ይህ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር በመላው ክፍለ ከተሞች፤ ወረዳዎች እና በየማዕከል እንደሚካሄድም ተናግረዋል።

ይህ ማዕድ ምግብ ብቻ ሳይኾን ፍቅር እና ክብር፣ ፈጣሪ እንኳን በሰላም ወደ አዲሱ ዓመት አሸጋገረን የምንልበት፤ ለከተማችን ነዋሪዎች ያለንን ክብር የምንገልጽበት ነው ብለዋል።

ክረምቱን ሙሉ ሲካሄድ የቆየው እና አሁን ከአዲሱ ዓመት መባቻ ጋር ተያይዞ የተከናወነው ይህ የበጎ አድራጎት ሥራ፣ በባለሀብቶች፣ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ነዋሪዎች እና በማኅበራት ትልቅ አስተዋጽኦ የተከናወነ እንደኾነ ገልጸዋል። በጎ ፈቃደኞቹም ላበረከቱት ድጋፍ ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ የኾኑ ዜጎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_04_2018_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኅይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበልዩነት ውስጥ አንድነት፤ በኅብረት ውስጥ አብሮነት ተገምዷል።
Next article‎🤝🎨 የጋራ እሴቶች፣ የጋራ ሀገር 🇪🇹