ባሕልን መጠበቅ ትውልድን መቅረጽ እና ማንነትን ማስቀጠል ነው።

12
በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ የእንግጫ ነቀላ በዓል ዞናዊ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር በተለያዩ ባሕላዊ ዝግጅቶች ተከብሯል።
ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች በልጃገረዶች የሚከበረው የእንግጫ ነቀላ በዓል፤ ልጃገረዶች በነፃነት የሚጫወቱበት፣ በስንኞች መልካም ምግባር ያላቸውን የሚያመሠግኑበት እና ተገቢ ያልኾነ ጠባይን የሚያርሙበት ልዩ ባሕላዊ ክዋኔ ነው።
በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ ልጃገረዶች በጭፈራ፣ በዕልልታ እና በባሕላዊ ጨዋታዎች ማሳለፋቸውንም ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዕድሜዓለም አንተነህ ባሕልን መጠበቅ ትውልድን የመቅረጽ፣ ሥርዓትን የማስተማር እና ማንነትን የማስቀጠል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የእንግጫ ነቀላ በዓል እና ሌሎች አካባቢያዊ ባሕላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉ በትኩረት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
በበዓሉ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ ባሕላዊ ምግቦች ለዕይታ የቀረቡ ሲኾን በተለያዩ ክዋኔዎች ታጅቦ ተጠናቅቋል።
ዘጋቢ፦ ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ የሚናገሩበት ጊዜ አሁን ነው” አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክሂን
Next articleኢትዮጵያ እና ጽናት የማይነጣጠሉ ናቸው