“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ የሚናገሩበት ጊዜ አሁን ነው” አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክሂን

9
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክሂን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “AMECO Africa” የሚል ገጽ ከፍቶ የአሕጉራዊ ሚዲያ ሽፋኑን ለማስፋት የያዘውን አቅጣጫ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በዓለም አቀፍ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ የአፍሪካ ሁነቶች እና ባሕሎች በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኀን ለረጅም ጊዜ በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ሲቀርቡ እንደነበር ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ግን ታዳሚዎች ስለ አሕጉሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ እና ባሕል ትክክለኛ እና ተጨባጭ መረጃ የሚፈልጉበት ጊዜ ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።
“አፍሪካውያን አፍሪካን እና እውነታዋን ለዓለም የሚያቀርቡበት ጊዜ አሁን ነው” ያሉት አምባሳደሩ አሚኮ (AMECO) ያካበተው የጋዜጠኝነት ልምድ እና ሙያዊ ብቃት ይህንን አህጉራዊ ተልዕኮ በስኬት ለመወጣት እንደሚያስችለው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ በአንድነት እንየው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article‎በጽኑዎች የተጠበቀች፣ በጽናትም የኖረች
Next articleባሕልን መጠበቅ ትውልድን መቅረጽ እና ማንነትን ማስቀጠል ነው።