‎”ጽናትን ከትጋት፣ ትጋትን ከውጤታማነት፣ ውጤታማነትንም ከዘላቂ ብልጽግና ጋር ማቀናጀት ይገባል” አቶ ይርጋ ሲሳይ

14
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ጳጉሜን ሦሥት የጽናት ቀንን በማስመልከት የተቋሙን እና የዘርፎችን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ የጽናት ቀንን ስናከብር በችግሮች ውስጥ ያሉንን አቅሞች ለይተን በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በተከታታይ ጥረት ወደ ውጤት የምንቀይርበት እና የጀመርናቸውን የልማት ጉዞዎች በትጋት ለማስቀጠል ቃል በመግባት ነው ብለዋል።
የዛሬ ጽናት ለነገ ሁለንተናዊ ስኬት መሠረት ነው ያሉት አቶ ይርጋ በተጠናቀቀው በ2018 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የታየው የመሪዎች እና የባለሙያዎች ቅንጅት፣ የሥራ ስነ ምግባር እና ቁርጠኝነት በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስኬት በአጋጣሚ የሚመጣ ሳይኾን በየዕለቱ በሚደረግ ትጋት እና ጽናት የሚገነባ መኾኑን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸማችን ምስክር ነው ብለዋል።
ጽናትን ከትጋት፣ ትጋትን ከውጤታማነት፣ ውጤታማነትንም ከዘላቂ ብልጽግና ጋር ማቀናጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የዛሬ ጥረታችንን ለነገ ስኬታችን ወሳኝ በመኾኑ በጋራ በመትጋት ለክልላችን እና ለሀገራችን የተሻለ ነገን እንገንባ ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየበጎነት እና የጽናት ምሣሌው ቢኒያም በለጠ!
Next article‎በጽኑዎች የተጠበቀች፣ በጽናትም የኖረች