
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን ቀጥለዋል።
ታጣቂዎቹ ሲጓዙበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን በመገንዘብ የሰላም አመራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።
በወረዳው ከአሁን በፊትም በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬም በወረዳው በምሥራቁ ቀጣና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 52 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ከደባርቅ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች፣ የደባርቅ ወረዳ እና የሰሜን ጎንደር ዞን የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
#ለዘላቂሰላም_የሰላም_አማራጭን መቀበል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
