
የምዕራብ ጎጃም ዞን ጳጉሟን ሦሥት የጽናት ቀንን ከጸጥታ አባላት ጋር በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች አክብሯል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ምክትል አዛዥ ኮማንደር አዳምጣቸው ዓለሙ ሀገር እንድትጸና የፖሊስ ሠራዊቱ ያለምንም መዛነፍ በመስዋዕትነት የታጀበ ቁርጠኝነቱን እየተወጣ መኾኑን አንስተዋል።
ቀደምት አባቶች ያጸኗትን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር ሁልጊዜም በትጋት እየሠሩ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሚሊሻ መምሪያ ኀላፊ መንግሥቱ ተስፋዬ የሚሊሻ ኀይሉ ከሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ውድ ሕይወቱን እየሰጠ የሕዝብን እና የሀገርን ደኅንነት እያረጋገጠ መኾኑን አንስተዋል።
ሰላሙን ለማጽናት በአንድ በኩል የኅብረተሰብ አደረጃጀትን ማጠናከር በሌላ በኩል የጸጥታ መዋቅሩን ለተሻለ ግዳጅ የማብቃት ሥራ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አዱኛ አዳሙ ያልጸና ትውልድ ሀገርን ያፈርሳል፤ ለጠላት አሳልፎ ይሰጣል ብለዋል።
በዞኑ ተፈጥረው የነበሩ ሁለንተናዊ ችግሮችን የጸጥታ መዋቅሩ በጽናት ቀልብሷቸዋል፤ ቀጣይም ይህን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
ዞኑ ከነበረበት የጸጥታ ችግር እንዲወጣ በጥቂት የጸጥታ መዋቅር የተጀመረው የሰላም ማጽናት ሥራ አሁን ላይ የተረጋጋ የሰላም ሁኔታ እንዲፈጠር እንዳስቻለ አስገንዝበዋል።
የጽናት ዋጋን በተግባር በማሳየት የጸጥታ መዋቅሩን በማደራጀት ሀገርን ለማሻገር በትጋት የመሥራቱ ተግባር ይጠናከራል ብለዋል።
#አሚኮ#ጽናት #ፍኖተሰላም #Ethiopia🇪🇹
#ፍኖተ_ሰላም #ጳጉሜን_03_2018_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ ፦ ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
