
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የበዓላት ወቅት ሲደርስ የኦንላይን ገበያ እና የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር ይጨምራል። ይህም በጥሬ ገንዘብ ከመገበያየት የተሻለ ደህንነትን ይፈጥራል።
ነገር ግን አታላዮች በኢንተርኔት፣ በኢሜይል፣ በጽሑፍ መልእክት እና በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎችን እና ገንዘብን ለመስረቅ መሞከራቸው የተለመደ ነው።
ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል (INTERPOL) በበዓላት ወቅት ይበረክታሉ ያላቸውን የዲጂታል ወንጀሎች ጠቅሶ የጥንቃቄ ምክረ ሃሳቦችን አስቀምጧል።
✍️በበዓላት ወቅት የተለመዱ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች፦
#የበዓላት ቅናሽ እና ሀሰተኛ የገበያ ድኅረ ገጾች፦ ታዋቂ የንግድ ድርጅቶችን በመምሰል እቃዎችን በተጋነነ ቅናሽ እንሸጣለን በሚል ሀሰተኛ ድኅረ ገጾችን ያዘጋጃሉ። ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ እቃውን አይልኩም።
#አሳሳች መልዕክቶች (Phishing)፦ “የበዓል ስጦታ ወይንም እጣ ወጥቶልዎታል” ወይም “እቃ በአየር መንገድ ወይንም በፖስታ ቤት ተልኮሎዎታል” የሚሉ አሳሳች ሊንኮችን በመላክ ምስጢራዊ የባንክ መረጃዎችን ይዘርፋሉ።
#የበዓል የበጎ አድራጎት ማጭበርበር፦ ለተቸገሩ ወገኖች እርዳታ ለማሠባሠብ በሚል እና ሀሰተኛ የበጎ አድራጎት ጥሪዎችን በማቅረብ ገንዘብ ይሰበስባሉ።
#የቴክኒክ ድጋፍ እና የሀሰት ደረሰኞች፦
ያልገዟቸውን የበዓል ስጦታዎች እንደገዙ የሚያሳይ ሀሰተኛ ደረሰኝ በመላክ ወይም “መሳሪያዎ በቫይረስ ተጠቅቷል” በማለት የኮምፒዩተርን የሩቅ መቆጣጠሪያ (Remote Access) ይጠይቃሉ።
ራንሰምዌር (Ransomware)፦ አጠራጣሪ ሊንኮችን ወይም ፋይሎችን ሲከፍቱ መሳሪያዎን በመቆለፍ መረጃዎችን ለመልቀቅ ገንዘብ ይጠይቃሉ።
✍️መፍትሔ
#አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመንካት፦ ካልታወቁ ምንጮች የሚላኩ የበዓል ቅናሽ ሊንኮችን፣ አባሪ ፋይሎችን ወይም የመልእክት ጥሪዎችን አለመክፈት።
#የድኅረ ገጾችን ሕጋዊነት ማረጋገጥ፦ መረጃ ከማስገባትዎ በፊት የድኅረ ገጹን አድራሻ (URL) እና የፊደላት አጻጻፍ በትክክል ማረጋገጥ።
#ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) መጠቀም፦ ለሁሉም የኦንላይን እና የባንክ አካውንቶች ተጨማሪ የደኅንነት ሽፋን መተግበር ይገባል።
#የባንክ እንቅስቃሴን መከታተል፦ የበዓል ግዢ ሲፈጽሙ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሪፖርትን አዘውትሮ ማረጋገጥ።
✍️ይሄም ኾኖ ችግሩ ቢከሰትስ?
#ለፋይናንስ ተቋማት ማሳወቅ፦ ወዲያውኑ ለባንክ በመደወል የባንክ ካርድን ወይም አካውንትን ማስወገድ።
#ለሕግ አስከባሪዎች ማመልከት፦ ለፖሊስ ወይም ለሳይበር ወንጀል መከላከል ክፍል የደረሰውን ችግር በተመለከተ ሪፖርት ማድረግ ይመከራል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
