ከቃል ባለፈ የተግባር ውጤት።

10

 

በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት “የማንሠራራት ቀን” በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በዝግጅቱ ወቅት በዋና ዋና የልማት ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያሳዩ የፎቶ አውደርዕይ እና ዶክመንተሪ ለዕይታ ቀርቧል።

የርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ አብደላ ኑሩ እንደገለጹት ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገርም ኾነ እንደ ክልል ለወደፊት ዕድገት መሠረት የሚኾኑ ዐበይት ድሎች ተመዝግበዋል።

በበጋ መስኖ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ በመኸር ሰብል ልማት የምርት እና ምርታማነት ዕድገት ተመዝግቧል ነው ያሉት።

የሕዝቡን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ ታላላቅ የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውንም አንስተዋል።

በተከናወነው የኮሪደር ልማትም ከተሞች ለኑሮ ተስማሚ፣ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ እንዲኾኑ ተደርጓል ነው ያሉት።

ለማዕድን ዘርፉም በተሰጠው ልዩ ትኩረት እምቅ ሃብቱን በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ መኾን እንደጀመረም አስገንዝበዋል።

የንጹሕ መጠጥ ውኃ እና የታዳሽ ኀይል አቅርቦትን ተደራሽ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ሥራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።

ከቱሪዝም አንጻር አዳዲስ መዳረሻዎችን በማልማት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ሚና ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በተካሄደው የፓናል ውይይት የርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ የግብርና፣ የመንገድ፣ የቱሪዝም፣ የማዕድን፣ የውኃ እና ኢነርጂ፣ የከተማ ልማት ቢሮዎች መሪዎች ተሳታፊ ኾነዋል።

#አሚኮ #ልማት #አማራክልል #Ethiopia🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጳጉሜን የሕሊና እና የውስጥ ማንነት መታደሻ ማድረግ ይገባል።
Next articleየአማራን ሕዝብ ወሰን እና ማንነት ጥያቄ አሳልፈው ላለመስጠት የሰላም አማራጭን መከተላቸውን የቀድሞ ታጣቂ መሪዎች ገለጹ።