
በአማራ ሕዝብ የማንነት እና ወሰን ጥያቄ ስም የሚደረጉ የተሳሳቱ እንቅስቃሴዎችን በመቃወም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሕዝቡ መቀላቀላቸውን በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአፋብን ከፍተኛ መሪዎች ተናግረዋል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት በጫካ በተሳሳተ መንገድ መቆየታቸውን የጠቀሱት የአፋብን የሃብት ልማት ምክትል ኀላፊ በለጠ አዱኛ ወደ ጫካ የገቡት የሕዝብን ጥያቄዎች ለማስመለስ አልመው እንደነበር ጠቅሷል። ከዚህ አላማ በተቃራኒ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን እና የሕዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ አካሄድ በመኖሩ የመንግሥትን የሰላም አማራጭ መምረጣቸውን ገልጿል።
የእርስ በእርስ መገዳደል መፍትሔ እንደማያመጣ በመጠቆም ከመንግሥት ጋር በመኾን የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን አረጋግጧል። ሌሎች ታጣቂዎችም ወደ ሰላም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ለታጣቂዎቹ አቀባበል ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጌታቸው ሙሉጌታ እና የጠገዴ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጋሻው ፍታለው የታጣቂዎቹን ውሳኔ አድንቀዋል።
መሪዎቹ በጫካ ያሉ አደረጃጀቶች የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈም ሀገር ለማፍረስ እየሠሩ መኾኑን ተረድተው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለስ ሀገርን እና ሕዝብን የሚያስቀድም ትክክለኛ ውሳኔ መኾኑን ገልጸዋል።
#አሚኮ #ሰላም_ወልቃይትጠገዴ #አማራክልል #Ethiopia🇪🇹
#ሁመራ #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
