ጳጉሜን የሕሊና እና የውስጥ ማንነት መታደሻ ማድረግ ይገባል።

12

 

በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር 13ኛዋ ወር ጳጉሜን የቀን መቁጠሪያ መሸጋገሪያ ብቻ ሳትኾን የሕሊና እና የውስጥ ማንነት መታደሻ ወቅት መኾን እንዳለባት የሃይማኖት አባቶች አስገንዝበዋል።

የአቡሻኸር እና የብሉይ ኪዳን መምህሩ አክሊሉ ብርሃኑ እንደገለጹት ጳጉሜን በዘመን አቆጣጠር ውስጥ ራሷን የቻለ ቀመርና አቆጣጠር ያላት ልዩ ወር ናት።

በዚች አጭር ወር ታዲያ ኢትዮጵያውያን ከእርስ በእርስ ጦርነት፣ ከግጭት እና ከመለያየት ወጥተው ለሰላም ሊዘጋጁ ይገባል ነው ያሉት።

የብሉይ ኪዳን መምህሩ ዳንኤል ብርሃኑ በበኩላቸው በአሮጌው ዘመን የነበረውን መለያየት በመቀራረብ፣ ጥላቻውን ደግሞ በፍቅር እና በመዋደድ ለመተካት በጳጉሜን ቀናት መዘጋጀት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዓመት መቀየር ብቻ ሳይኾን የሰው ልጅ ውስጣዊ ማንነቱ መታደስ እንደሚያስፈልገውም ነው ያስገነዘቡት።

አዲሱን ዓመት የተቸገሩትን በመርዳት፣ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ማክበር ይገባልም ብለዋል።

#አሚኮ #ሰላም #ዋግኽምራ #አማራክልል #Ethiopia🇪🇹

#ሰቆጣ #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየተመዘገበው የመንገድ መሠረተ ልማት ዕድገት የክልሉን የማንሰራራት ጉዞ የሚያሳይ ነው።
Next articleከቃል ባለፈ የተግባር ውጤት።