የተመዘገበው የመንገድ መሠረተ ልማት ዕድገት የክልሉን የማንሰራራት ጉዞ የሚያሳይ ነው።

6

 

በአማራ ክልል በመንገድ መሠረተ ልማት ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ዕድገት የክልሉን የማንሰራራት ጉዞ በተጨባጭ የሚያሳይ መኾኑን የክልሉ መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ ገልጿል።

የቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) እንደገለጹት ቀበሌዎችን፣ ወረዳዎችን እና ዋና ዋና የመንገድ መስመሮችን ለማስተሳሰር በተከናወኑ ሥራዎች የክልሉን የመንገድ ሽፋን ከ36 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ማድረስ ተችሏል።

በተጨማሪም ነባር መንገዶችን በመጠገን፣ በርካታ የኮንክሪት እና ተንጠልጣይ ድልድዮችን በመገንባት የአርሶ አደሮችን የምርት ማጓጓዝ ሂደት እና የሕዝቡን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ተችሏል ብለዋል።

የመንገድ መሠረተ ልማቱ መስፋፋት የገጠር እና የከተማ ትስስርን ከማጠናከሩ ባሻገር የትራንስፖርት ወጭን እና የጊዜ ብክነትን በመቀነስ እንዲሁም የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የመንገድ መሠረተ ልማት የልማት አቅምን የሚወስን ቁልፍ መሠረተ ልማት በመኾኑ፣ በዘርፉ የታየው ዕድገት የክልሉ የማንሰራራት ጉዞ በተግባር እየተረጋገጠ መምጣቱን የሚያሳይ ተጨባጭ ማረጋገጫ መኾኑንም ዶክተር ጋሻው አመላክተዋል።

#አሚኮ #የመንገድ_መሠረተልማት#አማራክልል #Ethiopia🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን በመንገድ መሠረተ ልማት ስኬታማ ያደረጋት ምንድን ነው ?
Next articleጳጉሜን የሕሊና እና የውስጥ ማንነት መታደሻ ማድረግ ይገባል።