ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን በመንገድ መሠረተ ልማት ስኬታማ ያደረጋት ምንድን ነው ?

20
🛣️
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ለመንገድ መሠረተ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች። በዚህም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
✅ ከከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2010 ዓ.ም ከነበረው የ126 ሺህ 773 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን በ2018 ዓ.ም ወደ 180 ሺህ 232 ኪሎ ሜትር አድጓል።📈
✅ ለስኬታማነቱ ምክንያቶችም ተቋማዊ አደረጃጀትን በማጠናከር፤ ለመንገድ መሠረተ ልማት የሚመደበውን በጀት በማሳደግ፤ በአጭር ጊዜ ፕሮጀክት የመፈጸም አቅምን በማዳበር፣ ጠንካራ የክትትል እና ድጋፍ ሥራዎችን መተግበር መቻሉ በአብነት ይጠቀሳሉ።
🎯 እስከ አሁን ድረስ የተመዘገበውን በመንገድ መሠረተ ልማት የማንሠራራት ጉዞ በማላቅ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሀገሪቱን የመንገድ ሽፋን ወደ 245 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማድረስ በዕቅድ ተይዟል።
📌 የሀገሪቱን የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴን የሚያቀላጥፉ የፍጥነት መንገዶችም በከፍተኛ ፍጥነት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
👉 ለአብነትም አዲስ አበባ-አዳማ፣ ሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ እና ድሬዳዋ-ደዋሌ ያሉ የፍጥነት መንገዶች ተገንብተው አገልግሎት በመሰጠት ላይ ናቸው።
👉 ከዚህ የተገኘውን ልምድ በማስፋት በቀጣይም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ተሠርቶ እንደተጠናቀቀ መረጃዎች ያሳያሉ።
👉 በተጨማሪም ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ እና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
📌 ከዋና ዋና መንገዶች በተጨማሪ በተቀናጀ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ መርሐ ግብር የገጠር እና የከተማ ትሥሥርን የሚያጠናክሩ ክልልን ከክልል፣ ዞንን ከዞን፣ ወረዳን ከወረዳ እና ወረዳን ከቀበሌ የሚያገናኙ በርካታ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።
📌 ከኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ገር በማስተሳሰር በከተሞች ምቹ እና ዘመናዊ የመንገድ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሠራው ሥራም በበርካታ ከተሞች ውጤታማ የመንገድ ልማት ተሠርተዋል።🏙️
👉 ለአብነትም በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መግለጻቸው ይታወሳል።
በዚህም ባለፉት ዓመታት አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት፣ በማስፋፋት፣ በመጠገን እና በዘመናዊ የመንገድ ተደራሽነትን በማስፋፋት ኢትዮጵያ የማንሠራራት ጉዞዋን አጠናክራ ቀጥላለች።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleከውድመት ወደ ማንሰራራት – አዲሱ የምዕራብ ጎጃም ገጽታ
Next articleየተመዘገበው የመንገድ መሠረተ ልማት ዕድገት የክልሉን የማንሰራራት ጉዞ የሚያሳይ ነው።