የአማራ ክልል የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

19

 

የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ በክልሉ የሚከበሩ የክረምት የአደባባይ በዓላት መዝጊያ መርሐ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ቡሄ፣ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ነቀላ፤ አሱሪቴ፣ ከሴ አጨደ እና አቡር ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ሲከበሩ ቆይተዋል።
የአደባባይ በዓላቱ የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ የሚያነቃቁ፤ ማኅበራዊ አብሮነትን የሚያጎለብቱ፤ ባሕል እና እሴትን የሚጠብቁ ናቸው።

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፤ የበዓላት ሁነቶችን ተሳታፊ ልጃገረዶች፤ ታዋቂ ሰዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#አሚኮ#Tourism #ኢትዮጵያ
#ባሕርዳር #ጳጉሜን01/2018 ዓ.ም

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🇪🇹 የኢትዮጵያ የእመርታ ጉዞ ወዴት?
Next articleየክረምት በዓላት የአዲስ ዓመት የብሥራት ምልክት ናቸው።