በደቡብ ጎንደር ዞን ሰላምን ሲያውኩ የነበሩ ጽንፈኞች ተደመሰሱ።

36

 

በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር አንድ መቶ ሰባት ፅንፈኞችን ተከታትሎ ደምስሷል። ኮሩ ከነሐሴ 01 አስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ባካሄደው የተቀናጀ የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 51 ፅንፈኞች ሲደመሰሱ፣ 24 ቆስለዋል፣ 32 በተለያየ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኮሩ ባካሄደው ሕግ የማስከበር እርምጃ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ ተተኳሾች፣ የመገናኛ ሬድዮዎች እና ከኅብረተሰቡ ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ከተደመሰሱት መካከል፣ ግዜ ግርማ የተባለ የፅንፈኛዉ ቡድን የአንዳቤቴ ብርጌድ የነሱ መዋቅር ፍርድ ቤት ኀላፊ፣ ሙጨ ታምር የአንበሳዉ ጋይንት ክፍለ ጦር አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ፣ ሽሻነዉ ጠጋ የአንበሳዉ ጋይንት ሻለቃ አዛዥ ይገኙበታል።

የፅንፈኛዉን የጥፋት ዓላማ የተረዱ 12 አመራርና አባላት የሰላምን አማራጭ ተቀብለዉ የገቡ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ ቻሌ አለባቸዉ የእስቴ ዴንሳ በነሱ አጠራር ኮር ዘመቻ የነበረ እና አማረ ደሴ ሞላ ሻለቃ መሪ የነበረ ይገኙበታል። ታጣቂዎቹ እንደተናገሩት፣ በፊት የፅንፈኛውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመከተል እና በመደናገር ገብተው ነበር። አሁን ላይ ግን እውነታውን በየዕለት ሥራዎቹ ስለተረዱና ቡድኑ የሚሠራውን ግፍ በቅርበት ስላዩ፣ ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እንዋጋለን እያለ ግን ሕዝብን ሰላም እያሳጡ እንደኾነም ስለተረዱ የጽንፈኞችን ሥራ ሙሉ በሙሉ ጠልተነዋል ብለዋል። ሰላም ይሻላል በማለትም የሰላምን አማራጭ ተቀብለው መግባታቸውን ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባካሄደው ፀረ-ሽምቅ ስምሪት የደቡብ ጎንደር የፀጥታ ኃይል፣ መሪዎች እና ሰላም ወዳዱ ሕዝብ ከፍተኛ ሚና መጫዎታቸውም ተገልጿል።

መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።

#አሚኮ #Defencenews #Ethiopia
#ነሐሴ29/2018ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጭና ግፍ እና የትውልድ የቤት ሥራ
Next articleየዓባይ ነገር – ወዲህ ለሕልውና፣ ወዲያ ለከንቱ ሴራ