
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታዳጊ ሀገራት የኤሌክትሪክ፣ የኢንተርኔት እና የክህሎት ክፍተቶቻቸውን በፍጥነት ከደፈኑ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ታግዘው በምዕተ ዓመት ያቀዱትን የልማት ጉዞ በአስርት ዓመታት ውስጥ ማሳካት እንደሚችሉ የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት አረጋግጧል።
ታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ለመኾን ግዙፍ የዳታ ማዕከላትን መገንባት አይጠበቅባቸውም። አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሣሪያዎችን ከአካባቢያቸው ነባራዊ ኹኔታ ጋር በማስማማት የሕክምና፣ የትምህርት፣ የፍትሕ እና የግብርና አገልግሎቶችን ማዘመን እንደሚችሉ ተጠቅሷል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለታዳጊ ሀገራት ያመጣቸው ዋና ዋና ዕድሎች፦
#የሥራ እድል እና የምርታማነት እድገት፦ በበለጸጉ ሀገራት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ 14 ነጥብ 2 በመቶ የሥራ ዕድሎችን የመተካት ሥጋት አለው።
በታዳጊ ሀገራት ግን ይህ ሥጋት 4 ነጥብ 5 በመቶ ብቻ ነው። በአንጻሩ በታዳጊ ሀገራት 16 ነጥብ 2 በመቶ የሚኾኑ የሥራ ዘርፎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዘው ከፍተኛ የምርታማነት እድገት ያሳያሉ።
በመኾኑም የዓለም ባንክ ግኝት እንደሚጠቁመው ከኾነ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዋነኛ ጥቅም ሠራተኞችን መተካት ሳይኾን የሠራተኞችን የሥራ አቅም ማሳደግ ነው።
#የሕዝብ አገልግሎቶችን ማፋጠን፦ የባለሙያዎች እጥረት ባሉባቸው ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሐኪሞች የበሽታ ምርመራን፣ ለገበሬዎች የሰብል እንክብካቤ ውሳኔን፣ ለመንግሥት ተቋማት የታክስ አሠባሠብን እና የማኅበራዊ ድጋፍ መርሐ ግብሮችን ለማቀላጠፍ ይረዳል።
ነገር ግን የዓለም ባንክ ለ300 ሚሊዮን አፍሪካውያን ሃይል ለማዳረስ እየሠራ መኾኑ ትልቅ ተስፋ ነው።
በቴክኖሎጂው ውጤታማ ለመኾን ሀገራት ምን ያድርጉ?
#ተቀብሎ መጠቀም፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሠሩ ዝግጁ የAI መሣሪያዎችን ሥራ ላይ ማዋል፤
#ማስማማት፦ መሣሪያዎቹን ከአካባቢው ቋንቋ፣ ባሕል እና ፍላጎት ጋር ማጣጣም፤
#ማሳደግ፦ የረጅም ጊዜ አቅምን በመገንባት የራስን የሠው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ማልማት ለውጤት እንደሚያበቃ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
