በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።

5
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።
በወረዳው ከአሁን በፊትም በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬም ተጨማሪ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የደባርቅ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ሲጓዙበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።
ከደባርቅ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የነበሩበትን የጥፋት መንገድ በመተው ወደ ኅብረተሰቡ እና ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ መወሰናቸውንም አስታውቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“በእጃችሁ የያዛችሁት ስማርት ስልክ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ነው” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)
Next articleሰው ሰራሽ አስተውሎት ለታዳጊ ሀገራት ምን ዕድል አመጣ?