
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናትን ስያሜ እና አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ ኢትዮጵያ ካሏት ልዩ ቀናት መካከል የጳጉሜን ቀናት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
የጳጉሜን ወር ያለፈውን ዓመት ሥራዎቻችንን የምንገመግምበት፤ የሚቀጥለውን ዓመት ዕቅድ እና ተስፋም የምንሰንቅበት ልዩ ወር ስለመኾኑም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የጳጉሜን ወር ቀናትን በልዩ ስያሜ እያከበረች ነው። ይሄም ዜጎች የግል ዕቅዳቸውን ከሀገራዊ አቅጣጫ ጋር በማስተሳሰር ለሀገር ልማት የበኩላቸውን እንዲወጡ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።
በዚህ ዓመትም አምስቱም የጳጉሜን ቀናት በጋራ “የኢትዮጵያ ማንሠራራት” በሚል መሪ ቃል ይከበራሉ ነው ያሉት። ይህም በእርግጥም የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያሳዩ ተጨባጭ ለውጦች የተመዘገቡበት ለመኾኑ ማሳያ ነው። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀበት፣ ግዙፉ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ የተጀመረበት እና ሌሎችም ዐበይት ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ስለመኾኑም ለአብነት አንስተዋል።
እያንዳንዱ ቀናት የራሳቸው ስያሜ ተሰጥቷቸው የሚከበሩ ሲኾን በዚህም መሠረት፦
ይህንን ጽናት ማስቀጠል የዛሬው ትውልድም ኀላፊነት መኾኑን ለማስገንዘብ ነው ቀኑ “የጽናት ቀን” ተብሎ የሚከበረው። በቀኑም ከጥዋቱ 12:00 ላይ በመላው ኢትዮጵያ እና በኢምባሲዎችም ጭምር በሁሉም የመንግሥት እና የግል ተቋማት የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ምልክት የኾነውን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረግ ብሔራዊ መዝሙር ይዘመራል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
