
በዓለም ላይ ተወዳጅ፤ ተፈላጊ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝነት አለው። ሕንድ፤ ቻይና እና መሰል ሀገራት በስፋት በማምረት ለምግብነት ይጠቀሙበታል። በኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ባይሰጠውም በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት የሩዝ ሰብል ይመረታል።
በአማራ ክልል የሩዝ ምርት በስፋት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች የደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ አንዱ ነው። በወረዳው በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከምርት ባሻገር የተደላደለ ሕይወት እንዲኖሩ ዕድል እየፈጠረላቸው ነው።
በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት በሚደገፈው በኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት አጋዥነት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ለማዕከሉ የላብራቶሪ አቅርቦትን በማሟላት፤ ከእርሻ ጀምሮ እስከ ማቀናበር የሚደርሱ ቴክኖሎጅዎችን በማቅረብ፤ አነስተኛ የማቀነባበሪያ ማሽኖችን በማሟላት እገዛ ማድረጉን አንስተዋል።
ከ40 በላይ የሩዝ ዝርያዎች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ እንደየ አካባቢው የአየር ንብረት መሠረት ዘር እንደሚሠራጭም ተናግረዋል።
የሩዝ ምርት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ተረፈ ምርቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።
ገለባው ለእንስሳት መኖ፤ ለኀይል ምንጭ፤ ለምግብ ማብሰያ ማገዶ እና ለተለያዩ ተግባራት እንደሚያገለግልም ገልጸዋል።
የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል ተመራማሪ ሰገድ አይቸው ከደቡብ ጎንደር በተጨማሪ በተለያዩ ዞኖች የሩዝ ልማትን ማስፋት ተችሏል ብለዋል።
ከኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር 500 ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን በመያዝ የተጀመረው የሩዝ ልማት አሁን ላይ 6 ሺህ 285 አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጅ በማገዝ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
አርሶ አደሮች በራሳቸው ዘር እንዲያባዙ እና በአቅራቢያቸው ለሚገኙ አርሶ አደሮች እና ለምርጥ ዘር ድርጅቶች እንዲያቀርቡ መደረጉንም አንስተዋል።
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት አሥተባባሪ አለባቸው አሊጋዝ ወደ ልማት ያልገቡ አካባቢዎችን ወደ ልማት በማስገባት፤ አርሶ አደሮችን በማሠልጠን፤ የዘር ሥርዓቱን በማሻሻል የሩዝ ምርትን ለማሳደግ ተሠርቷል ብለዋል።
ከተለያዩ የምርምር ጣቢያዎች የሩዝ ዘርን በማምጣት ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ውጤታማ እንዲኾኑ መሠራቱን ገልጸዋል።
አርሶ አደሮች የሩዝ ምርትን ጥቅም በመረዳታቸው ተጠቃሚ ከመኾናቸው ባሻገር የምርት ሽፋኑ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። የሩዝ መፈልፈያ ማሽኖችን ለአርሶ አደሮች ይበልጥ ለማቅረብ እየተሠራ ነውም ብለዋል።
በባለሙያዎች የሚደረግ ድጋፍ እና የምርታማነት መጨመር በዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲኾኑ ዕድል እየፈጠረላቸው መኾኑንም ገልጸዋል።
ከዘልማድ አሠራር በመውጣት በቴክኖሎጅ ታግዘው በማልማታቸው ለቤተሰብ የሚያስፈልገውን ግብዓት እንዲያሟሉ፤ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ፤ ለገበያ በማቅረብ ሕይወታቸውን እንዲለውጡ እና በዘርፉ ስኬታማ እንዲኾኑ ማስቻሉንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
