ብሔራዊ ዲጂታል የጤና ሥርዓት ሀገሪቱን ወደ አዲስ የዲጂታል ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው።

6
በጤናው ዘርፍ የሚደረጉ የዲጂታል እንቅስቃሴዎችን በተቀናጀ መንገድ ለመምራት የሚያግዝ ብሔራዊ ዲጂታል የጤና ሥርዓት ይፋ ተደርጓል።
የጤና ሚኒስትር ድኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ባለፉት ዓመታት የጤና ሥርዓቱን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በርካታ መዋለ ነዋይን በማፍሰስ በመሠራቱ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።
አስተማማኝ የመረጃ ልውውጥ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ የመረጃ አጠቃቀም እና የውሳኔ አሰጣጥ አቅምን ማጎልበት መቻሉን አንስተዋል።
የሚተገበረው ብሔራዊ ዲጂታል የጤና ሥርዓትም በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ እና ከፋይዳ ጋር የተናበበ ስለሚኾን በተበጣጠሰ መንገድ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ አንድ ምህዳር የሚያመጣ ነው ብለዋል።
ዲጂታል የጤና ሥርዓቱ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ትንተና በመስጠት ጊዜያዊ ሳይኾን ተለዋዋጭ በኾኑ ሁኔታዎች ሁሉ መሻገር የሚችል ተደርጓል ነው ያሉት።
ብሔራዊ ዲጂታል የጤና ሥርዓቱ ሀገሪቱን ወደ አዲስ የዲጂታል ምዕራፍ የሚያሸጋግር መኾኑን ነው የገለጹት።
ይፋ የተደረገው ብሔራዊ ዲጂታል የጤና ሥርዓት​ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለሌሎችም ሀገራት ተሞክሮ የሚኾን፣ የጤና መረጃዎችን እና ሥርዓቶችን እንዴት ማቀናጀት እንደሚቻል ማሳያ ነው ተብሏል።
መረጃዎችን በማጋራት አገልግሎቶችን በማቀናጀት እና በጋራ በመሥራት ዘላቂ እና ውጤታማ የጤና ሥርዓት ለመገንባት መሠረት የሚጥል መኾኑም ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለአራት ተከታታይ ዓመታት ሁሉንም ተማሪዎች ያሳለፈው የሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
Next articleእውነት የማትሞትበት የዋርካው ጥላ።