የኃይሌ ማናስ አካዳሚ ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 38ቱ የውጭ የትምህርት እድል አገኙ።

19
ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው ኃይሌ ማናስ አካዳሚ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች መቶ በመቶ ማሳለፉን አስታውቋል።
ከተፈታኞቹ መካከል 88 በመቶ የሚኾኑት የውጭ ሀገራት የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን አስታውቋል።
በ2013 የትምህርት ዘመን መማር ማስተማር የጀመረው አካዳሚው ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ ያስፈተናቸውን 43 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፉን የኃይሌ ማናስ አካዳሚ ምክትል ዳይሬክተር ተስፋዬ ክፍሌ ተናግረዋል።
እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል 30 የሚኾኑት ከ500 በላይ አስመዝግበዋል። 38 ተማሪዎች ደግሞ በውጭ ሀገራት ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ የትምህርት ዕድል አግኝተዋል።
በዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና ከተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪ ናትናኤል ክንደዓለም 570 ነጥብ 25 በማምጣት የአካዳሚው የከፍተኛ ውጤት ባለቤት ነው። ሻሎም ከፈለኝ 548 ነጥብ 83 በማስመዝገብ ከሴት ተፈታኞች በአካዳሚው የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች።
አካዳሚው ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፉ ይታወሳል።
✍️ ዘጋቢ:- ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበሀገር አቀፍ ፈተና በሴቶች አንደኛ የኾነችው ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑ ሽልማት ተበረከተላት።
Next article“በባዕዳን ተልዕኮ ያልተሰናከለው የኢትዮጵያ ስኬት”