
1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ ) የመውሊድ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር መስጊድ በድምቀት ተከብሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ መሐመድ ሸሪፍ ከተማዋ የሃይማኖት መቻቻል፤ የአብሮነት እና የአንድነት ከተማ እንዲትኾን ሕዝበ ሙስሊሙ ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። ሕዝበ ሙስሊሙ የተቸገሩ ወገኖችን በአይነት እና በገንዘብ በመደገፍ የብዙዎችን ሕይወት ታድጓል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ረጅም ጊዜ ጦርነት ላይ የነበሩ አካላት ጦርነትን እንዲያቆሙ እና ሰላምን እንዲመርጡ ያደረጉ ናቸው ብለዋል። ዛሬ የልደት ቀናቸውን በድምቀት እያከበርን እንገኛለን ነው ያሉት።
ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አንድነትን እንድናጠናክር መክረዋል፤ ሰላምን ሰብከዋል፤ እኩልነት እንዲረጋገጥ አድርገዋል፤ የልደት ቀናቸውን ስናከብርም የእርሳቸውን አስተምሮ በመከተል ሊኾን ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
