76ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባዔ (RC76) በአዲስ አበባ ከተማ ተጀመረ።

5
በጉባዔው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ ሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
የጉባዔው ዋና አላማ አሕጉራዊ የጤና ስትራቴጂዎችን ማደራጀት፣ በበሽታዎች መከላከል እና ቁጥጥር ላይ የጋራ ውሳኔ ማሳለፍ ነው ተብሏል።
ጉባዔው አሕጉሪቱ ዘላቂ የጤና ፋይናንስ የመገንባት፣ የቁጥጥር ሥርዓቶችን የማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ መድኃኒት እና ክትባት ምርትን የመጨመር እንዲሁም ኢቦላ እና መሰል ወረርሽኞችን የመቋቋም አዲስ አቅጣጫ ለመንደፍ ይመክራል ነው የተባለው።
ዘጋቢ፦ መሠረት መቅጫ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleዕዝነት፣ እኩልነት እና ፍትሕ የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመሪነት ጥበብ
Next articleመውሊድ፦ የደግነት በዓል